በመድረኩ በዋናነት የኮሌጁ የቀጣይ 10 አመት ስትራቴጂ እቅድ እንዲሁም የተቋሙ የሰው ሀይል ልማት ረቂቅ ሰነድ ለኮሌጁ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላትና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይቶች ተካሂደዋል::
ኮሌጁን በቀጣይ አመታት ግልፅ በሆነ ስትራቴጂ ለመምራት የሚያስችል አቅም የሚፈጥር የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱን ያስታወቁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ ይህ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድም ሰፊና ብዙ ጉዳዮችን በውስጡ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ መጪውን ዘመንም ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በመሆኑ መሪ እቅዱን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ያለመ መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ከፌደራል በተሰጠን ተልዕኮ መሰረት አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂክ እቅድ ለህብረተሰቡና ለኢንዱስትሪው እንዲወርድ አቅጣጫ መሰጠቱን አስታውሰው የዘርፉን እስትራቴጂ በተቋም ደረጃ ስናወርድ ምን ምን ተግባራት ይከናወናሉ የሚለውንም የሚመልስ እስትራቴጂክ እቅድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ የዘርፉን እስትራቴጂክ እቅድ ከተቋማችን የ10 ዓመት እስትራቴጂክ እቅድ ጋር የምናስተዋውቅ ይሆናል ብለዋል::
በመድረኩ የኮሌጁን የ10 አመት እስትራቴጂክ እቅድ በኮሌጁ የእቅድና በጀት ዝግጅት ባለሙያ በሆኑት አቶ አለማየሁ ብርሃኑ እማካኝነት ለባለድርሻ አካላት የቀረበ ሲሆን በዚህም ኮሌጁ እንደ አንድ የትምህርትና ስልጠና ተቋም ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር በቀጣይ 10 አመታት በትኩርት የሚያከውናቸውን ቁልፍ ጉዳዮች በዝርዝር ለመድረኩ ተሳታፊዎች ገለፃ ማድረግ ተችሏል::
በቀረቡት ረቂቅ ሰነዶች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህም የስትራቴጂክ እቅዱ ከኢንዱስትሪው አኳያ ታሳቢ ያልተደረጉና መካተት ይገባቸዋል ያሉዋቸውን ገንቢ ሀሳቦችም በመድረኩ አንስተዋል::
በቀጣይ የኮሌጁ የ10 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተገኙ ግብዓችን አካቶ ለኮሌጁ ቦርድ አቅርቦ በማፀደቅ ወደ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Join us social media
https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr







