በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) ድጋፍ::

  • April 3, 2026
  • Comment 0

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በአስተዳደሩ ዋሂል ክላስተር በSolar PV Installation & Maintenance ስልጠናዋን ተከታትላ ላጠናቀቀች ወጣት በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉ በዋናነት በBMZ ADRA, Germany አማካኝነት የተገኘ ሲሆን ይህም 1.1 KW የሚያመነጭ የSolar PV System ዝርጋታ እና በሶላር የሚሰራ ማብሰያ ምድጃ(Solar Cooker) ያካተተ እንደሆነም ተገልፇል::

በፕሮጀክቱ ድጋፍ የተደረገላት ወጣት ፎዚያ ባጋጠማት የአካል ጉዳት ሳትበገር ከምትኖርበት ከዋሂል ክላስተር ጁጁማ ወረዳ ተነስታ ኮሌጅ ድረስ ለስድስት ወራት 20 ኪሎ ሜትሮችን እየተመላለሰች ስትሰለጥን የቆየች ብርቱ ሴት ስትሆን የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክትም የዚህችን ወጣት ድካም በመረዳት በአካባቢዋ የራሷን ቢዝነስ ሰርታ ገቢ ምታገኝበትን የSolar PV System ዝርጋታ እንዲሁም በፀሀይ ሀይል የሚሰራ ዘመናዊ ማብሰያ(Solar Cooker) በድጋፍ መልክ አበርክቷል::

የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በSolar PV Installation Maintenance ወጣቶችን አሰልጥኖ የሙያ ባለቤት ከማድረግም ባሻገር ተደራጅተው ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊ ድጋፎችን ሁሉ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ያስታወሱት የADRA Germany ዋና ሀላፊ አቶ ዳዊት መሀሪ ሲሆኑ በድሬዳዋ ገጠር ክላስተር ላይ ለእህታችን ፎዚያ የተደረገው ድጋፍም ፕሮጀክቱ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽና አካታች መሆኑን ማሳያ ከመሆኑም በተጨማሪም የፕሮጀክቱ ከላይ እስከታች የሚገኙ ሀላፊዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ የመስራት ድምር ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል::

ወጣት ፎዚያ በበኩሏ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከብዙ ድካም እንግልት እንዳሳረፋት በመግለፅ በተደረገላት ድጋፍም የተለያዩ ገቢዎችን በማመንጨት የራሷንም ሆነ የቤተሰቦቿን ህይወት እንደምታሻሽል የገለፀች ሲሆን በአጠቃላይ ይህ ድጋፍ እውን እንዲሆን ያደረጉ ለADRA ፕሮጀክት ሀላፊዎችንና አስተባባሪዎች በሙሉ ምስጋናዋን አቅርባለች::

በእለቱ በነበረው የድጋፍ ርክክብ ላይ የADRA Germany, የADRA Ethiopia ሀላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና የኮሌጁ አመራሮች በቦታው ተገኝተው የተደረገውን ድጋፍ ውጤታማነት የተመለከቱ ሲሆን ወጣቷንም አበረታተዋል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

Telegram https://t.me/EIPC2001

Facebook https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *