በኮሌጁ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር ማካሄድ ተጀመረ::

  • March 6, 2026
  • Comment 0

በኮሌጁ ዲን በሚመራው በዚህ የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር በድጋፍና ክትትል ቡድኑ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች፣ ዋና ስራ ሂደቶችና የስራ ክፍሎች በግማሽ አመቱ በእቅድ አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በስልጠና ጥራት፣ በመረጃ አደረጃጀት፣ በሀብት ማፍራትና ግብዓት አጠቃቀም ላይ ባተኮሩ ነጥቦች መነሻነት ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ቁመና የሚገመግም የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር መሆኑም ተገልጿል::

የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋና አላማ በተቋሙ የሚገኙ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃርና ካስቀመጡት ግብ አኳያ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ክትትል ለማድረግና በአፈፃፀም ክፍተት የሚታይባቸውን ተግባራቶች ተለይተው ክፍተቶች እንዲሞሉ ድጋፍ የማድረግ ሲሆን በተጨማሪም የተሻለ አፈፃፀም ለታየባቸው ስራ ሂደቶችና ክፍሎች እውቅና በመስጠት ለሌሎች ሞዴል እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነው ተገልፇል::

በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ እስካሁን የአውቶሞቲቭ፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የአይ.ሲ.ቲ፣ የውድ ዎርክ እና የኮስትራክሽ ትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት የድጋፍና ክትትሉ የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም


Telegram https://t.me/EIPC2001

Facebook https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *