ሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድርን አስመልክቶ በኮሌጁ ምልከታ ተካሄደ::

  • June 5, 2026
  • Comment 0

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በካይዘን ፅንሰ-ሃሳብ መነሻነት እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትና ወቅታዊ አፈፃፀም ላይ ከፌደራል በመጡ ባለሙያዎች በዛሬው እለት ግምገማ ተካሂዷል::

የሀገር አቀፍ የካይዘን ውድድር አካል በሆነውና ከፌደራል በመጡ ባለሙያዎች በተካሄደው ምዘና በኮሌጁ የስራ ቦታን ምቹ ከማድረግ ፤ ብክነትን ከመቀነስ፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ፍጥነትን ከማሻሻል አኳያ በተቀመጡ መመዘኛዎች የተከናወኑ ተግባራትንም ገምግሟል::

የምልከታ ቡድኑ በኮሌጁ የካይዘን ትግበራ አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርትን የተመለከት ሲሆን ከ8ቱ የውጤት አመላካች አኳያ የተገኙ ውጤቶችን በሪፖርቱ ተመልክተዋል::

በማስቀጠል ቡድኑ በተቋሙ የሚገኙ የስራ ክፍሎችና የስልጠና ወርክሾፖች ላይ የተከናወኑ የካይዘን ትግበራዎችን ከመመልከት በተጨማሪ የካይዘን ትግበራው ውጤታማነትና የተገኘውን ለውጥ የሚያመላክቱ ሰነዶችን በዝርዝር የገመገመ ሲሆን በኮሌጁ በትግበራ ወቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችንም መመልከት ችሏል::

“ዛሬን እናሻሽል፤ ብክነትን እንቀንስ፤ ጥራትና ፍጥነትን እንጨምር፤ ነገን እንገንባ”!!

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *